በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበጎ አድራጎት ድርጅቱ 110 ፍልሰተኞችን ከባህር ላይ ታደገ


ፎቶ ፋይል፦ ፍልሰተኞች ሜድትራኒያን ባህር ላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች እርዳታ እየሰጧቸው
ፎቶ ፋይል፦ ፍልሰተኞች ሜድትራኒያን ባህር ላይ የነፍስ አድን ሰራተኞች እርዳታ እየሰጧቸው

ከሜድትራኒያን ባህር ላይ መቶ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን መታደጉን አንድ የጣሊያን በጎ አድራጊ ድርጅት በለቀቀው ቪዲዮ አስታውቋል፡፤

“ኢመርጀንሲ” የተባለው የጣልያን በጎ አድራጊ ድርጅት ትናንት ሐሙስ 110 የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ከባህር ላይ እንደታደገ አስታውቋል።

የድርጅቱ የህክምና ቡድን የጤና ትኩረት ለሚሹ ፍልሰተኞች ክብካቤ ማድረጉም ታውቋል።

ፍልሰተኞቹ ከሰሜን አፍሪካ ወደ ጣልያን ሊገቡ በመሞከር ላይ እንደነበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት ፍልሰተኞቹ የህይወት አድን ተግባር በምታከናውን መርከብ ላይ ሆነው ወደ ጣሊያን በማቅናት ላይ ናቸው ተብሏል።

XS
SM
MD
LG