በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ሁለት የአሜሪካ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጣለች


ሎክሂድ ማርቲን ሎጎ
ሎክሂድ ማርቲን ሎጎ

ሎክሂድ ማርቲን እና ሬይቲዎን የተሰኙት የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋራጮች ለታይዋን መሣሪያዎችን በማቅረባቸው ቻይና የንግድና የመዋዕለ ነዋይ ማዕቀብ እንደጣለችባቸው ትናንት አስታውቃለች።

እርምጃው ቻይና እንደግዛቷ የምትቆጥራትን ታይዋን ለመነጠል የምታደርገውን ጥረት መቀጠሏን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

የአገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር ትናንት እንዳስታወቀው ኩባንያዎቹ ወደ ቻይና ምርትን ከማስገባት እንዲሁም አዲስ መዋዕለ ነዋይን ከመጀመር ታግደዋል ብሏል፡፡

ማዕቀቡ በሎክሂድ ማርቲን እና ሬይቲዎን ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያስከትል ግልጽ አይደለም ሲል የአሶስዬት ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች ለቻይና እንዳይሸጡ ያገደች ቢሆንም፣ አንዳንድ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋራጮች ግን በሌሎች መዋዕለ ነዋይ ዘርፎች በቻይና ይሳተፋሉ።

ቻይናና 22 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት ታይዋን እ.አ.አ 1949 ላይ ከተደረገ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ተለያይተዋል። የቻይናው ኮሚኒስት ፓርቲ ግን አስፈላጊ ከሆነ በጉልበትም ቢሆን መልሶ የማዋሃድ ግዴታ እንዳለበት ይናገራል።

ዩናይትድ ስቴትስ ኦፊሴላዊ የሆነ ግንኙነት ከታይዋን ጋር ባይኖራትም፣ ሰፋ ያለ የንግድና ኢመደበኛ ግንኙነቶች ግን አሏት። ዋሽንግተን ታይዋንን እንድትከላከል የፌዴራል ሕግ ያስገድዳል።

XS
SM
MD
LG