በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳንና እየጋመ የመጣው ሁከት


የተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ
የተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ

በደቡብ ሱዳን ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ላይ ሁከት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ነበር ሲል በአገሪቱ የሚገኘው የተመድ ተልዕኮ ሪፖርት ማደረጉን የተባበሩት መንግሥትታት ድርጅት ቃል አቀባይ ትናንት ኒው ዮርክ ላይ አስታውቀዋል፡

ሁከቱ በአብዛኛው አፐር ናይል፣ ዋራፕ እና ጆንግሌ ግዛቶች ላይ ታይቶ እንደነበር ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

በሁከት የተጎዱት ሰዎች ቁጥር በ87 በመቶ ጨምሮ እንደነበር በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተመድ ተልዕኮ በሩብ ዓመት ሪፖርቱ አመልክቷል ብለዋል ቃል አቀባዩ ስቴፋን ዱጃሪክ። ጠለፋ በ464 በመቶ፣ ከግጭት ጋር የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት ደግሞ 360 በመቶ ጨምሮ እንደነበርም ታውቋል።

በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትና የሰብዓዊ ሕግጋት መሠረት የደቡብ ሱዳን መንግስት ለግጭቱ መፍትሄ ለመስጠትና ሲቪሎችን ከጥቃት ለመታደግ በአስቸኳይ እንዲንቀሳቀስ ተልዕኮው ጥሪ አቅርቧል።

ተልዕኮው በተጨማሪም ሰላምን በተመለከተ ውይይት በማድረግና በመቶ የሚቆጠሩ ቅኝቶችን በማድረግ እንዲሁም በአንዳንድ ቦታዎች ግዜያዊ ጣቢያዎችን በማቋቋም ላይ መሆኑን አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG