በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ሽፍቶችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመረች


ኬንያ ሽፍቶችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመረች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

ኬንያ ሽፍቶችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመረች

የኬንያ ደህንነት ኃይሎች ከሰሜን ስምጥ ሸለቆ አካባቢ ሽፍቶችን የማጽዳት ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችንም ይዘዋል፡፡ ተችዎች በፖሊስ ተደግፎ የሚመራው የሠራዊቱ ዘመቻ ላልተገባ የሰብአዊ ጥቃት ሊያጋልጥ ይችላል ይላሉ፡፡

በሠራዊቱ የሚደገፈው የኬንያ ፖሊስ፣ በስምጥ ሸለቆ አካባቢ ማኅበረሰቡንና የጸጥታ ኃይሎችን የሚያጠቁትንና የሰዎችን ከብቶች የሚሰርቁትን ሽፍቶች ለመደመሰስ ዘመቻዎችን እያካሄደ ነው፡፡

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በኬኑክ ግዛት ቱርካና ወረዳ ውስጥ በተካሄዳባቸው የደፈጣ ጥቃት ሶስት ፖሊሶች ከተገደሉና ሌሎች ስምንት ሰዎች ከቆሰሉ በኋላ የዘመቻውን ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

ሽፍቶቹ በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ማኅበረሰቦችን ለአስርት ዓመታት ሲያጠቁ የቆዩና ከብቶችንም የዘረፉ ሲሆን ለብዙዎቹ ግጭቶችም ተጠያቂዎች ሆነዋል፡፡

የኬንያ ፖሊስ ኃላፊ ጃፌት ኩሜ ባላፈው ማክሰኞ የቱርካና ወረዳን ከጎበኙ በኋላ የማኅበረሰቡ አባላት እርስ በርሳቸው መጠቃቃትን እንዲያቆሙ አሳስበዋል፡፡

“በዚህ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ምንም ምርጫ የላቸውም፡፡ አብረው መኖርን መማር አለባቸው፡፡” ያሉት ኃላፊው “ ይህ አንዱ ማኅበረሰብ ሌላኛውን የማጥቃት ልማድ እንዲቀጥል ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ ይህን የማቆም አቅሙም ሆነ ፍቃደኝነቱ አለን፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የደህንነትና ስትራቴጅክ ጥናት ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አህመድ መሃመድ፣ የሽፍቶቹ ፍላጎት ከብቶችን መዝረፍ ነው ይላሉ፡፡

አህመድ “ፖሊስምይሁን መደበኛ ጦር ምንም ዓይነት ብርቱ ኃይል ሊገጥማቸው አይችልም። አሁን ጠፍተዋል።” የሚሉት አህመድ “ ግን የት ሄዱ?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ “ወደ ከተማ በማቅናታቸው አሁን ብዙም አያስጨንቁህም። ከዚያ ለተወሰነ ጊዜ ብቻህን ትቆይና ዙሪያ ገባውን ትፈትሻለህ። መሳሪያ ያለበትን ለማወቅ ትጥራለህ። ሰዎችን በኃይል ብታስገደድም ከዚያ አታገኛቸውም። እነርሱ ወደ ከተማ ተመልሰው መደበኛ ሥራቸውን ቀጥለዋል።” በማለት ስለ ዘራፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ሽፍቶቹ እጃቸውን እንዲሰጡና መሳሪያዎቻቸውን እንዲያስረክቡ ሦስት ቀን ሰጥቷል፡፡ ባላፈው ሳምንት ተጠርጣሪዎቹ ሽፍቶቹ በቱርካና ወረዳ ውስጥ መንገደኞቹን ያጓጉዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ ጥይት በማርከፈከፍ አንድ ተማሪን ጨምሮ ሶስት ሰዎችን ገድለዋል፡፡

በደቡብ ፖኮት የህዝብ እንደራሴ የሆኑት ዴቭድ ፕኮሲንግ በማኅበረሰባቸውና በቱርካና ጎሳዎች መካከከል ስለተፈጠረው የአሁኑ ውጥረት ምክንያቱ ድርቅ መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ፕኮሲንግ ይህንኑ ሲያስረዱ “የግጦሽ ወይም የመጠጥ ውሃ አጠቃቀም አስመልክቶ የተቀመጠ ሥርዓት የለም፡፡ ስለዚህ ፖኮቶች ራሳቸውን ወደ ወንዙ ሊያስጠጉ ይችላሉ፡፡ ምናልባት ይህ ወንዝ ደግሞ ወደ በቱርካና አስተዳደር ስር የሚካለል ከሆነ ቱርካናዎች ስጋት ይገባቸዋል ወይም ወደ እኛ መሬት እየመጡ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ እነዚያም በተቃራኒው ያስባሉ፡፡ ብዙ ግጭቶች የሚኖሩት በዚህ ምክንያት ነው፡፡ አሁን በአካባቢው ለግጦሽ ሳር ያለው ፉክክር እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

በግጦሽና በእንስሳት በሚጠጡት ውሃ ላይ የተነሳው ግጭት በአካባቢው ውጥረት እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን በሲቪልና መንግሥት እንቅስቃሴዎችን እንዲገቱ አድርጓል፡፡

ኬንያ አሁን በአካባቢው በድርቅ ከተጎዱ አገሮች መካከል አንዷ ናት፡፡ ድርቁ ባሪንጎ፣ ሌኪፒያ፣ ሳምቡሩ፣ ምዕራብ ፖኮት እና ቱርካንን ጨምሮ 23 ወረዳዎች ላይ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡

መሀመድ መንግሥት የከብቶቹን ስርቆት ለማስቆም ለተጎዱ አካባቢዎች ተጨማሪ ሀብቶችንና ልማቶችን ማከናወን ይኖርበታል ይላሉ

“እነዚያ ማኅበረሰቦች በርካታ ከብቶችን አጥተዋል፡፡ በቁጥርም እጅግ በጣም ቀንሶባቸዋል፡፡ ስለዚህ ሌሎች ብዙ ከብቶችን የሚነዱት በተመለከቱ ጊዜ እነሱን ወደ መዝረፍ መሄዳቸው እርግጥ ነው፡፡

ድርቅና የአየር ንብረት ለውጡ ትልቅ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡ በወደፊቱ እቅድ ውስጥ መካተት ይኖርበታል የምንለው ለዚህ ነው፡፡ መንግሥት ስለ ልማት ማሰብ አለበት፣ ህይወትን ከከብት እርባታ ውጭ በማሰብ ሰዎች ዘላቂ ህይወታቸውን እንዲኖራቸው የሚረዱ ሌሎች አማራጮችን ሁሉ ማሰብ ይኖርበታል፡፡

ጸጥታ የማስከበሩ ዘመቻ ለሰዎቹ ከጥሩ ጎኑ ይልቅ ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው የገለጹት ፕኮሲንግ “በምዕራብ ፖኮት ከሚገኙ 16 ክፍለ ግዛቶች 3ቱ በጭንቅ ውስጥ ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ዘመቻዎችን ስትጀምር ሁሉን ሰው ወንጀለኛ ልታደርግ ትችላለህ፡፡ ያለፈው ወቅት ሁሉንም ማህበረሰብ ወንጀለኛ ያደረገ ነው፡፡ ሥጋቴ ያ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ “ ባላፈው አስገድዶ መድፈር ነበር፣ የረሀብ አደጋ ነበር መንገዶች ተዘጋግተው ነበር፡፡

ከጥቂት ወራት በፊት ቴዬቲ ውስጥ መንገዶችና 16 ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ብዙም ሰዎች ለጥቂት ሞተው ነበር፡፡” ሲሉም የነበረውን ሁኔታ አስታውሰዋል፡፡

የዘመቻው ዓላማ የተዘረፉ ከብቶችን ማስመለስ፣ ትላልቅ ጎዳናዎችን መጠበቅና ሰዎች እና ሸቀጦች በነጻ እንዲንቀሳቀሱ ማስቻል መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG