በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅም ማነስ አፍሪካን ለድርቅና ለጎርፍ አደጋዎች እያጋለጣት ነው


 የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅም ማነስ አፍሪካን ለድርቅና ለጎርፍ አደጋዎች እያጋለጣት ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:35 0:00

ስለ አየር ሁኔታ ትክክለኛ የሆነ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ባለመኖሩ የአፍሪካ ሀገራትን ለከፋ ድርቅ፣ ለጎርፍ መጥለቅለቅና ለአውሎ ነፋስ አደጋዎች እያጋለጣቸው እንደሆነ ተገለፀ፡፡

በአዲስ አበባ በተካሔደ 18ኛው የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ጉባኤ ላይ የተገኙት የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፔትሪ ታላስ፣ ግማሽ የሚሆኑት የድርጅቱ አባል ሀገራት ትክክለኛ የሆነ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው የሜትሮሎጂ ጉባኤው በአየር ሁኔታ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ተደራሽነት ላይ ትኩረት ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

የታዳጊ ሀገራትን የአየር ትንበያ ሥርዓት ለማዘመንና በቴክኖሎጂ ለማገዝም የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ለታዳጊ ሀገራት የ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት ማፅደቁን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ውሀና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ደግሞ በኢትዮጵያ እና በአጎራባች ሀገራት ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች ባጋጠመ ድርቅ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት ማለቃቸውን ገልፀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG