በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ተጨማሪ የመሣሪያ ድጋፍ ያስፈልጋታል ሲል ኔቶ አስታወቀ


ፋይል - አንድ የአየር ሀይል ቡድን አባል ምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ጥይቶችን በሳጥን ይዞ - የካቲት 9፣ 2023
ፋይል - አንድ የአየር ሀይል ቡድን አባል ምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ጥይቶችን በሳጥን ይዞ - የካቲት 9፣ 2023

ለዩክሬን የሚሰጠው የጦር መሣሪያ እንዲጨምርና አገሮች ቃል የገቡትን ታንክና ሌሎች ከባድ መሣሪያዎች እንዲያስረክቡ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሃፊ የንስ ስቶልትንበርግ ዛሬ ብራስልስ ላይ ጥሪ አድርገዋል።

በአሜሪካ የሚመራ የዩክሬን አጋሮች የሆኑ የኔቶ አባል አገራት መከላከያ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ቡድን ዛሬ ብራስልስ ላይ ሲመክር ውለዋል።

የኔቶው ዋና ጸሃፊ ለዜና ሰዎች እንዳሉት፣ ስብሰባው ወሳኝ በሆነ ወቅት በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ የዩክሬን አጋሮች ለአገሪቱ የሚሰጥውን ወታደራዊ ድጋፍ የሚጨምሩበትን ሁኔታ ይመክራሉ።

በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ዓመት እንደሚሞላው ያስታወሱት የንስ ስቶልትንበርግ፣ ፕሬዝደንት ፑቲን ለሰላም ዝግጁ አይደሉም ሲሉ ከሰዋል።

በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የዩክሬኑ መከላከያ ሚኒስትር ኦለስኪ ረዝኒኮቭ በትዊተር መልዕክታቸው እንዳሉት የእርሳቸው አጀንዳ ተጨማሪ የጦር መሣሪያ የሚገኝበት፣ ዩክሬንን ከአየር ጥቃት መከላከል የሚቻልበት እንዲሁም ለዩክሬን ኃይሎች ስልጠና የሚሠጥበት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።

XS
SM
MD
LG