በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሚችጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተከፈተ ተኩስ ሶስት ተማሪዎች ተገደሉ


የሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ቴሬዛ ውድሩፍ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጡ - የካቲት 14፣ 2023
የሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ቴሬዛ ውድሩፍ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጡ - የካቲት 14፣ 2023

በአሜሪካ በሚገኘው ሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ ትናንት ማምሻውን በተከፈተ ተኩስ ቢያንስ ሶስት ተማሪዎች ሲገደሉ አምስት የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል።

የዩኒቨርሲቲው የፖሊስ አዛዥ ዛሬ ማለዳ እንዳስታወቁት፣ በከፍተኛ ደርጃ የተጎዱት ተማሪዎች በሆስፒታል ይገኛሉ ብለዋል።

ተኩሱን በመክፈት የተጠረጠረው የ43 ዓመት ግለሰብ ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ውጪ በራሱ ላይ በተኮሰው ጥይት ሞቶ መገኘቱን አዛዡ ጨምረው ገልጸዋል።

ተጠርጣሪው የዩኒቨሲቲው ዓባል አለመሆኑ ታውቋል። ለምን ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢው እንደመጣ ግን ምርመራ በመደረግ ላይ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለ 48 ሰዓታት ማንኛውንም ዓይነት ግልጋሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG