በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ሽፍቶች ላይ ልትዘምት ነው


ፋይል - የኬንያ መከላከያ ሰራዊት አባላት
ፋይል - የኬንያ መከላከያ ሰራዊት አባላት

በድርቅ በተጠቃው የኬንያ ሰሜናዊ ክፍል በሽፍቶች የሚካሄደውን ግድያና የከብቶች ዝርፊያ ለማስቆም ሰራዊቱን እንደሚያሰማራ የአገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

በሰሜናዊው የስምጥ ሸለቆ ክልል ሽፍቶችና ዘራፊዎች ባለፉት ስድስት ወራት በፈጸሙት ጥቃት 100 የሚሆኑ ሲቪሎችና 16 የፖሊስ አባላት ህይወታቸውን አጥተዋል ሲል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።

የከብቶች ስርቆትና በግጦሽ መሬት ሳቢያ ግጭት መፈጠሩ በሰሜን ኬንያ ባሉ ማኅበረሰቦች ዘንድ የተለመደ ቢሆንም፣ ሽፍቶቹ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሰላማዊ ኬንያውያንና በሕግ አስከባሪ አካላት ላይ ጥቃታቸውን ጨምረው ት/ቤቶችንና የፖሊስ ተሽከርካሪዎችን አቃጥለዋል ብሏል የአገር ውስጥ ሚኒስቴሩ።

የሰራዊቱ ሥምሪት ጉዳይ በፓርላማው መጽደቅ ይጠበቅበታል።

በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸውን የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በመታወጁ ሕገ-ወጥ መሣሪያዎችን የያዙ ሰዎች በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት እንዲያስረክቡ ጥሪ አድርጓል።

በምሥራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ ተስፋ ተደርጋ የምትታየው ኬንያ አምስት የዝናብ ወቅቶች ደርቀው በማለፋቸው ከአርባ ዓመታት ወዲህ ያልታየ ድርቅና ቸነፈር እንስሶችንና ሰብሎችን አጥፍቷል።

XS
SM
MD
LG