በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ ጎርፍ 12 ሰዎችን ገደለ


ፋይል - የነፍስ አድን ሰራተኖች ታህሳስ 4፣ 2022 በጆሃንስበርግ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የተወሰዱ ሰዎችን ሲያፈላልጉ
ፋይል - የነፍስ አድን ሰራተኖች ታህሳስ 4፣ 2022 በጆሃንስበርግ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የተወሰዱ ሰዎችን ሲያፈላልጉ

በደቡብ አፍሪካ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ 12 ሰዎችን ከገደለ በኋላ ፕሬዝደንቱ ብሄራዊ የአደጋ ግዜ አዋጅ አውጀዋል።

ዝናቡ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ሲሆን፣ በደቡብ አፍሪካ ካሉ ዘጠኝ አውራጃዎች ውስጥ በአራቱ የሰዎችን ህይወት መቅጠፉን የአገሪቱ የአደጋ መከላከያ ቢሮ አስታውቋል።

ከሞዛምቢክ ጋር አዋሳኝ በሆነው ሥፍራ የሚገኘውና የቱሪስት መስዕብ የሆነው ክሩገር ብሄራዊ ፓርክ በጎርፉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ሲሉ የቢሮው ቃል አቀባይ ለኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

እስከትናንት ድረስ 7 ሰዎች እንደሞቱ ሲነገር የነበረ ቢሆንም፣ ቃለ አቀባዩ የሟቾቹ ቁጥር ወደ 12 መጨመሩን ተናግረዋል።

በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በቀን እስከ 20 ሴንቲ ሜትር ዝናብ እንደጣለ የአየር ንብረት ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

ጎርፉ ቤቶችንና ተሽከርካሪዎችን ሲወስድ፣ መንገዶችንና ድልድዮችን አፍርሷል።

የአገሪቱ ፕሬዝደንት በትናንትናው ዕለት ብሄራዊ የአደጋ ግዜ አዋጅ አውጀው ግዜያዊ መጠለያ፣ ምግብና አልባሳት ለተጎጂዎች እንዲደርስ አዘዋል።

XS
SM
MD
LG