በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎችን ወደ ናይጄሪያ ሊልክ ነው


ፋይል - አንድ የገለልተኛው ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን በሌጎስ፣ ናይጄሪያ በሚገኝ ክፍል ውስጥ የመራጮችን ቋሚ ካርድ ሲያስተካክል ይታያል - ጥር 12፣ 2023
ፋይል - አንድ የገለልተኛው ብሄራዊ ምርጫ ኮሚሽን ባለስልጣን በሌጎስ፣ ናይጄሪያ በሚገኝ ክፍል ውስጥ የመራጮችን ቋሚ ካርድ ሲያስተካክል ይታያል - ጥር 12፣ 2023

ከአስር ቀናት በኋላ በናይጄሪያ የሚደረገውን ምርጫ እንዲታዘቡ ዘጠና አባላት ያሉትን የታዛቢ ቡድን እንደሚልክ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቋል።

በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ በመጪው የካቲት 18 ቀን ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ ብትይዝም በነዳጅና በገንዘብ ዕጥረት ምክንያት ቅውስ ውስጥ ገብታለች።

የአፍሪካ ኅብረቱ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ የሚመራው በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ነው። ኬንያታ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት ቆሞ ስምምነት ላይ እንዲደረስ በሽምግልና ከተሳተፉት አንዱ ሲሆኑ፣ በምሥራቅ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ያለው ግጭት እንዲቆምም በማሸማገል ላይ ናቸው።

ኅብረቱ እንዳለው የልዑኩ ዓላማ ትክክለኛና ገለልተኛ የሆነ ግምገማ ለማድረግ፣ መሻሻል ያላባቸው ጉዳዩች ካሉ ሃሳብ ለመሠንዘር፣ እንዲሁም በናይጄሪያ ዲሞክራሲ፣ ሠላም፣ መረጋጋትና ልማት እንዲጠናከር ለማገዝ ነው።

ናይጄሪያ በጸጥታ እጦትና በኢኮኖሚ ድቀት ቀውስ በምትተራመስበት ግዜ በሚካሄደው ምርጫ 100 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ድምጻቸውን እንደሚሰጡ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ለሁለት የሥልጣን ዘመን አገሪቱን የመሩትን ሞሃማዱ ቡሃሪን የሚተካ መሪ ይመርጣሉ።

XS
SM
MD
LG