በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአማራ ክልል የተነሱ መንገደኞች አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገለፁ


ከአማራ ክልል የተነሱ መንገደኞች አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:14 0:00

ከአማራ ክልል የተነሱ መንገደኞች አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገለፁ

ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ የነበሩ መንገደኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ገለፁ።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት ተጓዦቹ “የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆነችው ጎሃ ፂዮን አካባቢ ስንደርስ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች እንድንመለስ አድርገውናል” ብለዋል፡፡

የካቲት 2 እና 3/2015 ዓ.ም የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ ተጓዦችን ብቻ ለይተው ይመልሱ እንደነበርና ከአርብ ወዲህ ግን ሁሉንም ተጓዦች መከልከላቸውን መንገደኞቹ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ተጓዦች ደጀን ከተማ ላይ እየተጉላሉነው መሆኑንም አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ከፌዴራል መንግሥት መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም፣ የኦሮሚያ ክልል አተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ፣ “የተዘጋ መንገድ የለም” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።

XS
SM
MD
LG