በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የአየር ጥቃት 12 የአል-ሻባብ አባላት ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፦የአል ሻባብ ተዋጊዎች
ፎቶ ፋይል፦የአል ሻባብ ተዋጊዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በማዕከላዊ ሶማሊያ ባደረገው የአየር ድብደባ 12 የአል-ሻባብ ተዋጊዎች መግደሉን ትናንት አስታውቋል።

አፍሪኮም የተሰኘው በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ እንዳለው “በጋራ ራስን ለመከላል የተፈጸመ” ያለውን የአየር ጥቃት ያከናወነው ባለፈው ዓርብ ሲሆን ይህም የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት በጠየቀው መሠረት የተከናወነ ነው ብሏል።

አፍሪኮም የጥቃቱን ትክክለኛ ሥፍራ ባይገልጽም፣ በመግለጫው ግን በደፈናው ከሞቃዲሹ ሰሜን በምሥራቅ አቅጣጫ 472 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ እንደተደረገ አስታውቋል።

የሶማሊያ መንግስት በበኩሉ በዓርቡ ጥቃት 117 ተዋጊዎች እንደተገደሉ አስታውቋል።

የሶማሊያ የእግረኛ ጦር አዛዥ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል ሞሃመድ ጣህሊል ቢሂ እንደገለጹት ተዋጊዎቹ የተገደሉት ከሶማሊያ መንግስት ጦር ጋር ፍልሚያ ላይ በነበሩበት ወቅት ነበር።

በጥቃቱ ሲቪሎች እንዳልተጎዱ አፍሪኮም ጨምሮ ገልጿል።

ባለፈው ዓርብ የተፈጸመው የአየር ጥቃት አሜሪካ “በጋራ ራስን ለመከላከል” በማለት በዓመቱ ያከናወነችው ሶስተኛው የአየር ጥቃት መሆኑ ነው።

XS
SM
MD
LG