በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን እስራኤል በፍትህ እቅዶቿ ዙሪያ ስምምነት ላይ እንድትደርስ ጥሪ አቀርቡ


ተቃውሞ ሰልፍ በእስራኤል
ተቃውሞ ሰልፍ በእስራኤል

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በመላው እስራኤል ተቃውሞ የቀሰቀሰውን እና በቤንጃሚን ኔታኒያሁ የቀኝ ዘመም መንግስት ግፊት የተደረገባቸውን የፍትህ እቅዶች ላይ ስምምነት እንዲኖር ጥሪ አቀረቡ።

ነገ ሰኞ የእስራኤል ፓርላማ በሕግ ማሻሻያ ዙሪያ ይሰባሰባል። ፓርላማው በሚኖረው የሕግ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይም የፍትህ ማሻሻያ በማድረግ፤ የጠቅላይ ፍርድቤቱን ሃይል በመቀነስ የህግ አስፈጻሚውን ሃይል የሚጨምረውን እና መንግስትን ዳኞችን የመምረጥ ሃይል የሚያጎናጽፈውን ሕግ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ ግፊት ታዲያ በመላው ሃገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን መንግስት የህግ ማሻሻያው ላይ ረጋ ብሎ ወደ ስምምነት እንዲደርስ ጥሪ እየተደረገ ይገኛል። የተለያዩ የህዝብ አስተያየት መስጫዎችም ህዝቡ ለእነዚህ ማሻሻያዎች ዝቅተኛ የሆነ ድጋፍ እንዳለው አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG