በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታጣቂዎች 10 የኒጀር ወታደሮችን ገደሉ ሲል የሃገሪቱ መከላከያ ሚንስቴር አስታወቀ


ኒጀር እና አጎራባች ሃገራት
ኒጀር እና አጎራባች ሃገራት

የኒጀር መከላከያ ሚኒስቴር ታጣቂ አሸባሪ ሲል በጠራቸው ቡድኖች በደቡብ ምዕራብ ኒጀር ከማሊ ድንበር አቅራቢያ በትንሹ 10 የሚደርሱ ወታደሮች መገደላቸውን ትላንት ቅዳሜ አስታውቋል።

ከትላንት በስቲያ አርብ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት 13 ወታደሮች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሌሎች 16 ደግሞ እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም። በዚህ የተነሳም የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎ አስታውቋል።

ወታደሮቹ በጊዜው በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ባኒባንጓ በተሰኘው አካባቢ ቅኝት በማድረግ ሳሉ ሃይማኖታዊ ጽንፈኛ በሆኑት ቡድኖች የተቀነባበረው የሽምቅ ጥቃት እንደደረሰባቸው ነው የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የተናገረው።

መግለጫው አያይዞም ከጥቃቱ ፈጻሚዎች በርካቶች መገደላቸውን አመልክቷል። ይሁን እንጂ ትክክለኛው አሃዝ አልተገለጸም።

XS
SM
MD
LG