በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪካ ከኃይል ምንጭ ቀውስ በተያያዘ የአደጋ ጊዜ አወጀች


የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ባለው አሽማድማጅ የኃይል ምንጭ ዕጥረት ምክንያት የአደጋ ጊዜ አውጀዋል። ዕጥረቱ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ኑሮ ላይ የህውልና አደጋ ደቅኗል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አሳስበዋል።

የመንግሥቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለሥልጣን መስሪያ ቤት በሀገሪቱ ታሪክ ታይቶ በሚያውቅ ደረጃ መብራት በማቋረጥ መኖሪያ ቤቶች ለጨለማ ተዳርገዋል። የፋብሪካዎቻና የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ስራም እየተስተጓጎለ መሆኑ ተዘግቧል።

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቆረጡ የሀገሪቱን ምጣኔ ሃብት የዚህ የአውሮፓ 2023 ዕድገት በ0 ነጥብ 3 ከመቶ እንደሚያቀጭጨው ተጠቁሟል።

በኤነርጂ ቀውሱ ላይ ብቻ አትኩረው የሚሰሩ የኤክትሪክ ኃይል ሚንስትር እንደሚሰይሙ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል። ከዚያም ሌላ በከፊል በለጋሾች ድጋፍ የሚከናወነውን የንጹህ የኃይል ምንጭ ሽግግር ሥራ እንቀጥላለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። ለዚህም በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የ84 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ነዋይ እንደሚመደብ ጠቅሰዋል።

XS
SM
MD
LG