በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ውስጥ የተፈጠረው ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ መንግሥት አቋም መያዙን የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሆኖም “አጋጣሚውን ለእኩይ የፖለቲካ ዓላማ ለመጠቀም የሚንቀሳቀሱ አካላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ የማቅረብ ተግባር ተጀምሯል” ብሏል።
በሌላ በኩል “መንግሥት የቤተክርስትያኒቱን ጥያቄ የማይመልስ ከሆነ ለየካቲት 5 የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል” ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ አስታውቋል።
የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል ትናንት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች በተመሳሳይ ቀንና ቦታ “ሕገወጥ” ሲል የገለጸው የሰልፍ ጥሪ መደረጉን ጠቅሶ ይህም ከሚመለከተው አካል አልተፈቀደም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ባወጣው መግለጫ ደግሞ “መንግሥት በግልጽ ወገንተኛ አቋም ይዞ በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገባ ነው” ብሎ ችግሩ ሰላማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ፡፡