ከኦሮሚያ ክልል አብዛኞቹም ከቄለም ወለጋ ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ጃራ መጠለያ ካምፕ ውስጥ በተከፈተ ተኩስ በተፈናቃዮችና በአካባቢው የጸጥታ ኃሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳን ከአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ ጋር በሚያጎራብተው ድሌ ሮቃ ቀበሌ ጃራ መጠለያ በአካባቢውና በአፋር ታጣቂዎች መካከል በትናንትናው ዕለት ተቀሰቀሰ በተባለው በዚህ የተኩስ ልውውጥ ተፈናቃዮች ከየትኛው ወገንና ምን ያህል እንደሆኑ ባናውቅም የሞቱና የቆሰሉ አሉ ብለዋል፡፡
የሰሜን ወሎ ፖሊስና ግጭቱ የተቀሰቀሰበት አካባቢ አመራር እንደሚሉት በትንሹ ሦስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ለህክምና ወደ ወልዲያ ተልከዋል፡፡
በአፋር ክልል የጭፍራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሊ አርባ የደረሰውን ጉዳት አጣርተው ይፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያው የሚገኙ አስተያየት ሰጭዎች ለዳግም ችግር ተጋልጠናል፣ ተገቢው የደህንነት ጥበቃ አልተደረገልንም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።