በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ መንገዶች ጥገና መጠናቀቁ ተገለፀ


ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ መንገዶች ጥገና መጠናቀቁ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:57 0:00

ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ መንገዶች ጥገና መጠናቀቁ ተገለፀ

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ መንገዶችና ድልድዮች የጥገና ሥራ ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ትግራይ የሚወስዱ መንገዶች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መደረጋቸውንም በተቋሙ የድልድይና የስትራክቸር ሥራዎች ዳይሬክተር ኢንጂነር ጌትነት ዘለቀ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር “ወደ ትግራይ ክልል በቅርቡ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት እያደረኩ ነው” ብሏል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ምክትል ሚን ኢስትር አቶ በረኦ ሐሰን “በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎቶችን እያስጀመረ ያለው ብሔራዊ ኮሚቴ ሲፈቅድልን አገልግሎቱን እናስጀምራለን” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ትራስፖርት ፈዴሬሽን በበኩሉ ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ማኅበራት ወደ ትግራይ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ እንደተላለፈላቸው አስተውቀዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG