በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ተመቶ ስለወደቀው ፊኛ ዩናይትድ ስቴትስን አጣጣለች

የዩናይትድ ስቴትስ ተዋጊ ጀት፣ ባላፈው ቅዳሜ በደቡብ ካሮላይና ግዛት አቅራቢያ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የታየውን የቻይና ስለላ ፊኛ መሆኑ የተጠረጠረውን መትተው ጥለዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ተዋጊ ጀት፣ ባላፈው ቅዳሜ በደቡብ ካሮላይና ግዛት አቅራቢያ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የታየውን የቻይና ስለላ ፊኛ መሆኑ የተጠረጠረውን መትተው ጥለዋል፡፡

ቻይና፣ ዩናይትድ ስቴትስ አየር ክልሏ ውስጥ የገባውን የቻይና ፊኛ መትታ ለመጣል መወሰኗ፣ ዋሽንግተን “የቻይናና አሜሪካን ግንኙነት ለማሻሻልና ለማረጋጋት ያላትን ቅንነት የሚፈትንና ቀውስን የምታስተናግድበት መንገድ የሚያሳይ ነው” ስትል ወቀሰች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ተዋጊ ጀት፣ ባላፈው ቅዳሜ በደቡብ ካሮላይና ግዛት አቅራቢያ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የታየውን የቻይና ስለላ ፊኛ መሆኑ የተጠረጠረውን መትተው ጥለዋል፡፡

ለበርካታ ቀናት ውቅያኖስን አቋርጦ በዩናይትድ ስቴትስ የየብስ አየር ክልል ላይ ሲጓዝ የነበረው ትልቅ የቻይና ፊኛ ፍጻሜው የሆነው በተዋጊው ጀት ተመቶ በመውደቁ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት ስለላና ቅኝት የሚያደርግ በረራ ብለው የገለጹት ፊኛ በአሜሪካ ሰማይ ላይ መብረሩ “ተቀባይነት የሌለውና ሉዐላዊነታችንን የጣሰ” የቻይና ተግባር ነው ብለውታል፡፡

አስተዳደሩ የወሰደው እርምጃ ፊኛው የአገሪቱን ክልል አቋርጦ ከገባ በኋላ መረጃ እንዳይሰብሰብ ለማድረግ ነው ሲሉ ባለሥልጣናቱ ጨምረው መግለጻቸው ተነግሯል፡፡

ቻይና የተባሉትን ክሶች ያስተባበለች ሲሆን የአየር ሁኔታን ለማጥናት የተሰማራ በስህተት ዩናይትድ ስቴትስ ክልል ውስጥ የገባ የሳይንስ መገልገያ መሳሪያ ነው ስትል ተከራክራለች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚ ፌንግ የፊኛውን መመታት አስመልክቶ ትናንት እሁድ በሰጡት መግለጫ “ የዓለም አቀፉን ልምድ የጣሰ አደገኛ” እርምጃ ነው ብለውታል፡፡

ፊኛው የአገሪቱን የአየር ክልል ጥሶ መግባቱ ከታወቀ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አነተኒ ብሊነክን ሁለት በኢኮኖሚ በገዘፉ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል በበጄኒግ ሊያደርጉ የነበረውን ጉብኘት መሰረዛቸው ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG