የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንተኒ ብሊንከን የሶስት ቀን ጉብኝታቸውን ለመጀመር በዛሬው ዕለት በመካከለኛው ምስራቅ ተገኝተዋል። ጉብኝታቸው የተጀመረው በእስራኤል እና ፍልስጤማዊያን መካከል አዲስ ግጭት በተቀሰቀሰበት ፣የኢራን እና የዩክሬን ውስጥ ጦርነት ጉዳይ በአጀንዳነት ዋና ስፍራን እንደሚይዝ በሚጠበቅበት ሰዓት ነው።ብሊንከን ካይሮ ላይ ከሚያደርጉት አጭር ቆይታ በኃላ ወደ እየሩሳሌም ሰኞ ዕለት ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በእስራኤል ቀኝ ዘመሙ የቤንያሚን ኔትኒያሁ አስተዳደር የመንግስት እና ኃይማኖት ልዩነት መርህ እሴቶችን፣ የላላው የጎሳዎች ግንኙነት እና ፍሬ አልባ ከፍልስጤማዊያን ጋር የሚደረግ የሰላም ንግግርን የመጪ ዘመን ዕጣን በተመለከተ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት አሳሳቢነትን ቀስቅሷል ።
በቅርብ ቀናት ውስጥ የተቀሰቀሰው የግጭት ደግሞ፣ የወትሮውን የግጭት አዙሪት ይበልጡኑ እንዳያባብሰው ስጋት ፈጥሯል ።
የዌስት ባንክ ሰፈራዎችን የማስፋፋት ፍላጎት ያላቸውን አክራሪ ብሄርተኞችን ካካተው የእስራኤል አስተዳደር ጋር በሚኖራቸው ንግግር ፣ ብሊንከን ፣ የዩናይትድ ስቴትስን በቀጠናው መረጋጋት ዳግም እንዲመለስ የሚጠይቅ ጥሪ ደግመው ያሰማሉ።ዋሺንግተን ለ"ሁለት -መንግስታት መፍትሄ" ያላትን ድጋፍ እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል። ይሁንና የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት በቅርብ ጊዜያት ረጅም ዕድሜ የሚኖረው የሰላም ንግግር የመምጣቱን ነገር እንደሚጠራጠሩ ያምናሉ።
ብሊንከን ወደ ራማላ በማቅናት ከፍልስጤም አስተዳደር ፕሬዚደንት ሞሃሙድ አባስ ፣ ሌሎች ፍልስጤማዊያን ባለስልጣናት እና የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ዘገባው የሮይተርስ ነው ።