በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶያማ ከተማ ውስጥ ስምንት ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች ሃያ ሰዎች መቁሰላቸውን ተከትሎ በቡርጂ እና በጉጂ ተወላጆች መካከል ለወራት ይሰማ ነበር የተባለው “ቂም ትናንት በተካሄደ እርቅ ተቋጭቷል” ሲሉ የሁለቱ አካባቢዎች ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች ገልፀዋል።
“ሰዎችን በማንነታቸው እየለዩ ገድለዋል” ተብለው የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሬ አለማየሁ አስታውቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ያገኛሉ፡፡