በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ የአየር ክልል የአያታን “ክላስ ኤ” ደረጃ አገኘ


አይኤቲኤ (አያታ) በሚል ምህጻር የሚጠራው ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ባለሥልጣን የሶማሊያን የአየር ክልል በ30 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ክላስ “ኤ” የሚባለው የደረጃ ምድብ ውስጥ ያስገባው መሆኑን አሳውቋል፡፡

ዕርምጃው በአካባቢው ደህንነትን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽል እና ስኬትን የሚያጠናክር መሆኑን “አያታ” የገለፀ ሲሆን ውሳኔው በአዲስ አበባ ሰዓት ባለፈው ዕኩለ ሌሊት ላይ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

“ምድብ ኤ” ደረጃ ከአማካይ የባህር ጠለል በላይ ከ24 500 ጫማ ከፍታ በላይ ያለው የአየር ክልል ሲሆን በዚያ ቀጣና ውስጥ የሚያልፉ በረራዎች ሁሉ ከምድር መቆጣጠሪያው ፈቃድ ማግኘት ፍቃድ ማግኘት እንደሚገባቸው እና ሞቃዲሾ የአየር መቆጣጠሪያም የሚያስፈልገውን መሣሪያ መግጠም እንዲችል የሚያደርገው እንደሆነ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG