የኦሮምያ ክልል ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ የሰላምና የፀጥታ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ችግር ለመቅረፍ የክልሉ መንግሥት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉ ፕሪዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ተገኝተው ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይም የሰላም እጦት ዋነኛ አጀንዳ እንደነበር ተናግረዋል።
የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ “ሸኔ” ብለው ከጠሩት ታጣቂ ቡድን በተጨማሪ “የአማራ ፅንፈኛ” ብለው የጠሩት ኃይል ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።
ኃላፊው “የአማራ ጽንፈኛ” ሲሉ ማንን ማለታቸው እንደሆነ አላብራሩም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የፈረጃቸውና “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች ቃል እንዲህ ያሉ ክሶችን እንደማይቀበሉ በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወሳል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።