በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በርካታ የዩክሬይን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሥራቸውን ለቀቁ


ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ
ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ

ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በመንግሥታቸው ውስጥ የአንዳንድ የሥራ ኃላፊዎች ለውጥ እንደሚኖር እየተናገሩ ባለበት ወቅት በርካታ የዩክሬን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሥራቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ።

ከምግብ ግዥ ጋር በተያያዘ የሚሰነዘርባቸውን የሙስና ቅሌት ክስ ያስተባበሉት የዩክሬንን ኃይሎች የሎጀስቲክስ ድጋፍ የሚቆጣጠሩት የሃገሪቱ ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ቪያቼስላቭ ሻፖቫሎቭ ሥልጣናቸውን ለቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አሌክሲ ሲሞኔንኮ እና የዜለንስኪ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ኪሪሎ ቲሞሼንኮም በተመሳሳይ የመልቀቃቸውን ምክንያት ሳይናገሩ ኃላፊነታቸውን ለቀዋል።

"በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ በሌሎች የማዕከላዊ የመንግሥት መዋቅሮች እንዲሁም በክልሎች እና በሕግ አስከባሪ አካላት ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ባለሥልጣናትን በተመለከተ.. የሰራተኞችን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ቀደም ሲል የተደረሰባቸው ውሳኔዎች አሉ።" ሲል ዘሌንስኪይ በትናንቱ የዘወትር ምሽት ንግግሩ ሰኞ አመልክተዋል። “... አንዳንዶቹ ዛሬ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ነገ ...” ነበር ያሉት የዩክሬይኑ ፕሬዚዳንት።

XS
SM
MD
LG