በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡርኪናፋሶ ውስጥ ታግተው የነበሩ ከስልሳ በላይ ሴቶች ተለቀቁ


ባለፈው ሳምንት በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ ስልሳ ስድስት ሴቶች እና ህጻናት መለቀቃቸውን የሃገሪቱ ብሔራዊ የዜና ማሰራጫ አስታወቀ።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2015 ዓም ከጎረቤት ማሊ የተስፋፋውን አደገኛ የእስላማዊ ጽንፈኞች ጥቃት እየተጋፈጠ ባለችው ቡርኪናፋሶ ይህን መሰል የጅምላ አፈና ካሁን ቀደም ታይቶ አይታወቅም።

ከሳምንት በፊት ነበር በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ ሳህል ክልሏ ሱም ግዛት፣ በአርቢንዳ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙት ሁለት መንደሮች ወጣ ካለ ሥፍራ ቁጥቋጦ ውስጥ ፍራፍሬ እና ቅጠላ ቅጠክ ለቀማ ላይ የነበሩትን ሴቶች እና ልጆቻቸውን ታጣቂዎች አግተው የወሰዱት።

የጸጥታ ኃይሎች ባካሄዱት የነፍስ አድን ዘመቻ ነው 27ቱን አዋቂ ሴቶች፣ 39ኙን ህጻናት እና እንዲሁም ወጣት ልጃገረዶቹን አጎራባች ግዛት ከሚገኝ ሥፍራ ያገኟቸው።

XS
SM
MD
LG