የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ወደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚያደርጉት ጉብኝት፤ ዓለም በመዓድን ሃብት በበለጸገችው ሃገር ላይ ላለፉት አስርት ዓመታት የተፈጸመውን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈውን ግጭት እንዳይዘነጋ የሚያስታውስ መሆኑን ወደ ኪንሻሳ የሚጓዘው የቫቲካን ልዑክ አስታወቀ።
ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስ ከሳምንት በኋላ ከጥር 22 እስከ ጥር 25/2015 ዓ.ም በጎንጎ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገልጿል። ይኸው ጉዞም እ.ኤ.አ በ1985 ከተደረገው የቫቲካን ጉብኝት በኋላ የመጀመሪያው ነው።
በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የካቶሊክ እምነት ተከታይ ያላት ግዝፏ ኮንጎም ሊቀ-ጳጳስ ፍራንሲስን ለመቀበል ሰፊ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።