በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተነጋገሩ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ትላንትናው ቅዳሜ ጥር 13/2015 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በህዳር ወር 2015 ዓ.ም የተደረገው የጦርነት ማቆም ስምምነት እስከአሁን ድረስ ባለው የአፈጻጸም ሂደት ላይ መነጋገራቸውን አስታውቋል።

በተመሳሳይ የውጭ ጉዳይ ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው ላይ በኢትዮጵያ ሰላም እና ተስፋን ለማስረጽ እየተሰራ ስላለው ስራ እና የኤርትራ ወታደሮች ለቆ መውጣትን በተመለከተ ተነጋግረናል ሲሉ አስፍረዋል።

የውጭ ጉዳይ ቢሮው ባወጣው መግለጫም ብሊንከን ይኸንን ለውጥ በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ የሆነ ሰላም ለማስፈን ቁልፍ ጉዳይ ነው ሲሉ ተቀብለውታል ያለ ሲሆን፤ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ቡድን ወደ ስፍራው እንዲገባ ፈቃድ እንዲሰጥ አሳስበዋል ብሏል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ‘በአፍሪካ ህብረት የተመራው የሰላም ስምምነት በሰሜን ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ እንዲረጋገጥ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች’ ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ አረጋግጠዋል ሲል መግለጫው አስታውቋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ባለስልጣናት በኦሮሚያ ክልል ባለው አለመረጋጋት ዙሪያ መነጋገራቸውንም መግለጫ አክሎ ያሰፈረው።

ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ በሁለቱ ባለስልጣናት ውይይት ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስት የተሰማ ነገር የለም።

XS
SM
MD
LG