በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ የስዊድን መከላከያ ሚኒስትርን የአንካራ ጉብኝት ሰረዘች


 የስዊድንና የቱርክ ከፍተኛ ባለሥልጣናት
የስዊድንና የቱርክ ከፍተኛ ባለሥልጣናት

ቱርክ የስዊድን የመከላከያ ሚኒስትር አንካራን ለመጎብኘት የነበራቸውን እቅድ መሰረዟን አስታወቀች።

ቱርክ ጉብኝቱን የሰረዘችው ስዊድን የቱርክ ተቃዋሚዎች ስቶኮሆልም ውስጥ በሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞ እንዲያደርጉ ፈቅዳለች በሚል መሆኑ ተገልጿል።

የቱርኩ መከላከያ ሚኒስትር ሁሉሲ አካር “የስዊድን መከላከያ ሚኒስትር ፓል ጆንሰን የፊታችን ዓርብ ጥር 19 2015 በቱርክ የሚያደርጉት ጉብኘት ምንም ትርጉም የማሰጥ ነገር ነው። ምክንያቱም ስዊድን የቱርክ ተቃዋሚዎች ያደረጉትን አስጸያፊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማስቆም እምርጃ መወሰድ ሲኖርባት የወሰደችው አንዳችም ርምጃ የለም፡” ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል።

ቱርክ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍና፣ በተቃውሞውም ወቅት ቅዱስ ቁርዓንን ለማቃጠል የነበረውን እቅድ አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡ በቱርክ የሚገኙ የስዊድን አምባሳደርን ትንናት ዓርብ ጠርታ ማነጋገሯ ተመልክቷል።

ስዊድን የኔቶ አባል ለመሆን የቱርክን ድምጽ የምትሻ ሲሆን፣ ቱርክም ስዊድን የቱርክን ተቃዋሚዎች በአገሯ እንዲንቀሳቀሱ መፍቀዱን ቀጥላበታለች በሚል ድምጿን መያዝዋ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG