በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጃኔት ዬለን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በሴኔጋል ጀምረዋል


የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ሚኒስትሯ ጃኔት ዬለን በዳካር ለወጣት እና ሴቶች የቢዝነስ ሰዎች ንግግር አስምተዋል ፣ ሴኔጋል ዳካር እኤኤ ጃንዋሪ 20 2021
የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ሚኒስትሯ ጃኔት ዬለን በዳካር ለወጣት እና ሴቶች የቢዝነስ ሰዎች ንግግር አስምተዋል ፣ ሴኔጋል ዳካር እኤኤ ጃንዋሪ 20 2021

በአፍሪካ የሚያደርጉትን የ10 ቀናት ጉብኝት በመጀመር ትናንት ዓርብ ሴነጋል የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ የግምጃ ቤት ሚኒስትሯ ጃኔት ዬለን፣ ዛሬ ቅዳሜ የሴኔጋሉን የጎሬ ደሴት ጎብኝተዋል።

ዬለን ደሴቲቱን ከጎበኙ በኋላ ባሰሙት ንግግር አትላንቲክ ውቅያኖስን ስለተሻገረው የባሪያ ንግድ “ሊገለጽ የማይችለው ጭካኔ” ሲሉ ተናግረዋል።

“የጎሬ ደሴት የአፍሪካና አሜሪካ ታሪኮች በጽኑ የተሳሰሩ መሆኑን ያስታውሱናል። አሳዛኙ ታሪክም ከዚህ በተወሰዱ ሰዎች ትውድል ብቻ የሚያበቃም አይደለም።” ብለዋል ዬለን።

ሚኒስትሯ ዛሬ ቅዳሜ ረፋዱ ላይ ከሴኔጋል ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል እንዲሁም ከፋይናንስ ሚኒስትሩ ማማዱ ባ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ተዘግቧል።

ሴኔጋል እንደብዙዎቹ አገሮች በአገር ውስጥ የዋጋ ንረትና ግሽበት የተመታች ሲሆን፣ ከፍተኛ የምግብ፣ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ ውድነት ያለባት መሆኑ ተገልጿል። ተነቃቅቶ የነበረው ኢኮኖሚዋም ዓለምን እያናጋ ባለው የሩሲያው የዩክሬን ጦርነት መጎዳቱ ተመልክቷል።

ዬለን በአየር ንብረት ቀውሱ ክፉኛ ከተጋለጡ 20 አገሮች መካከል 17ቱ የሚገኙት በአፍሪካ ነው ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አፍሪካ መር ለሆነው ለዚሁ ቀውስ ማስወገጃ የሚውል ከ1ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዳቸውንም የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ሚኒስትሯ ጃኔት የሌን ትናንት ዓርብ ማስታወቃቸው ተመልክቷል።

ሚኒስትሯ ዳካር ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉ የወጣትና የሴቶች ፕሮጀክቶችን የተመለከቱ ሲሆን ከሴነጋል በኋላ ወደ ዛምቢያና ደቡብ አፍሪካ እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

XS
SM
MD
LG