በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉግል 12 ሺህ ሰራተኞችን ከሥራ ሊያሰናብት ነው


የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ማውንቴን ቪው፣ ካሊፎርኒያ
የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ማውንቴን ቪው፣ ካሊፎርኒያ

የግዙፉ ቴክኖሎጂ ተቋም የጉግል እናት ኩባንያ አልፋቤት 12 ሺህ ሰራተኞች እንደሚያሰናብት አስታወቀ። ከጠቅላላው የኩባንያው የሰው ኃይል ስድስት ከመቶ መሆኑ ነው።

የአልፋቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሱንዳር ፒቻይ፣ዛሬ ለሰራተኞች በላኩት ኢሜል ኩባንያው ባለፉት ሁለት ዓመታት አስደናቂ እድገት በማሳየቱ አዳዲስ ሰራተኞችን የቀጠረው አእሁን ከተደቀነብን ለተለየ የኢኮኖሚ ዕውነታ ነበር” ብለዋል፡፡

አስከትለውም ኩባንያው ዛሬ ላለበት ሁኔታ ላበቁት ውሳኔዎች በሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስዱ አመልክተዋል።

ሰራተኞችን የመቀነስ ውሳኔ ላይ የተደረሰው የኩባኒያው ሰራተኞች እና የሥራ ድርሻቸው ጉግል በዋናነት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ጥልቅ የሆነ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚሰሩት የሚቀነሱ ሰራተኞች እንደተነገራቸው የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሌሎች ሀገሮች ያሉት ሰራተኞችን በሚመለከት ግን ሰራተኞች ግን በየሀገሩ ባሉት የተለያዩ ህጎች እና መመሪያዎች ምክንያት ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ እንደሚወስድ አስታውቀዋል፡፡

የፌስቡክ እና የኢንስታግራም እናት ኩባንያው ሜታ፣ ትዊተር፣ ማይክሮሶፍት እና አማዞን የመሳሰሉ ሌሎች ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞቻቸውን እንደሚያሰናብቱ በዚሁ ሳምንት ውስጥ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG