በደቡብ ክልል የሀላባ ዞን ነዋሪዎች በዞኑ ተስፋፍቷል ያሉትን ሙስና መንግሥት መርምሮ እርምጃ እንዲወስድ ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።
ተቃውሟቸውን በክልሉ ርዕሰ መስተደድር እና ፀረሙስና ኮሚሽን ቢሮ ፊት ያቀረቡት ሰላማዊ ሰልፈኞች፤ “የዞኑ ባለሥልጣናት የከተማን መሬት ይቀራመታሉ፣ የመንግሥትና የቀበሌ ቤቶችን በራሳቸውና በዘመዶቻቸው ሥም ያዘዋውራሉ፣ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ለግል ጥቅም ያውላሉ” ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።
ተሠርቷል ያሉትን ወንጀል ከጠቆሙና የተቃውሞ ሰልፍ ካካሄዱ ነዋሪዎች ውስጥም የታሰሩ እንዳሉ ገልፀዋል። የሀላባ ዞን ባለሥልጣናት ምላሽ እንዲሰጡን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። የደቡብ ክልል ፀረሙስና ኮሚሽን አቤቱታቸውን መቀበሉን ገልፆ ምርመራውን እንደሚቀጥል አስታውቋል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/