በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“እስራኤል ዌስት ባንክ ውስጥ ሁለት ፍልስጥዔማውያንን ገድላለች” ሲሉ የፍልስጥዔም ባለሥልጣናት ከሰሱ


የእስራኤል ወታደሮች በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ አካባቢ
የእስራኤል ወታደሮች በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ አካባቢ

የእስራኤል ወታደሮች “ዌስት ባንክ ውስጥ ዛሬ ጥቃት ከፍተው ሁለት ፍልስጥዔማውያንን ገድለዋል” ሲሉ የፍልስጥዔም ባለስልጣናት ክሥ አሰሙ።

ጃዋድ ባዋክናና አድሃም ጃባሪን የሚባሉት ፍልስጥዔማዊያን ጂኒን ከተማ ውስጥ ተተኩሶባቸው እንደተገደሉ የፍልስጥዔም የጤና ሚኒስቴር አመልክቷል።

ባዋክና መምህር እንደነበረ የፍልስጥዔም አስተዳደር የዜና ወኪል ዋፋ አስታውቋል። ታጣቂው የአልአክሳ ሰማዕታት ብርጌድ ደግሞ ጃባሪን ተዋጊው እንደነበረ ገልጿል።

የእሥራኤል የጦር ሠራዊት በወታደሮቹ ተገድለዋል ስለተባሉት ሁለት ሰዎች ጉዳይ አስተያየት አልሰጠም።

XS
SM
MD
LG