ቻይና የህዝቧ ብዛት ከስድሳ ዓመታት በኋላ እአአ ባለፈው 2022 ለመጀመሪያ ጊዜ መቀነሱን አስታወቀች።
የሀገሪቱ የስታቲስታቲክስ ቢሮ ባወጣው መረጃ መሰረት ባለፈው 2022 ዓመተ ምህረት 9 ነጥብ 56 ህጻናት የተወለዱ ሲሆን 10 ነጥብ 41 ሰዎች ሞተዋል። በዚያም ሂሳብ የህዝቡ ብዛት በ850 ሺህ ቀንሷል።
እአአ በ1950ዎቹ ዓመታት የማኦ ሴ ዶንግ የፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ፖሊሲ ሳቢያ በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ዜጎች በረሃብ ካለቀ ወዲህ የህዝቧ ብዛት ሲቀንስ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተመልክቷል።