በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታኒያ ፍልሰተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ያወጣችው ዕቅድ አዲስ የፍ/ቤት ሙግት ገጠመው


ፎቶ ፋይል፦ የተቃውሞ ሰልፈኞች ለንደን ከሚገኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት እአአ 12/19/2022
ፎቶ ፋይል፦ የተቃውሞ ሰልፈኞች ለንደን ከሚገኝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት እአአ 12/19/2022

የብሪታንያ መንግሥት ፍልሰተኞችን ወደሩዋንዳ ለመላክ ያለውን ዕቅድ በመቃወም የቀረበው ሙግት በሀገሪቱ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዲታይ ተወሰነ።

በርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የዕርዳታ ድርጅቶች እና የድንበር ጥበቃ ባለሥልጣናት ማኅበራት የመሰረቱትን ክስ ባለፈው ወር ሁለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች ውድቅ አድርገው አወዛጋቢው የመንግሥቱ ፖሊሲ ህጋዊ ነው የሚል ውሳኔ ሰጥተውበት ነበር።

ታዲያ ትናንት ሰኞ እነዚሁ ዳኞች ከሳሾቹ ውሳኔውን መቃወሚያ ክርክራቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቀዋቸዋል። ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሚሰየምበት ቀን አልተቆረጠም።

የብሪታኒያ መንግሥት ፍልሰተኞች ፈረንሳይ እና ብሪታንያን በሚለየው "ኢንግሊሽ ቻነል" በኩል ለማቋረጥ እንዳይሞክሩ ያደርግልኛል በማለት የሚገቡ ፍልሰተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ሥምምነት መፈራረሙ ይታወሳል። ባለፈው ዓመት ብቻ 45 ሺህ ፍልሰተኞች በባህር ወሽመጡ በኩል የገቡ ሲሆን ብዙዎች ባህሩ ላይ ህይወታቸውን አጥተዋል።

የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ብሪታኒያ "ፍልሰተኞችን ወደማይፈልጉት እና 6400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወዳለ ሀገር ለመላክ ያወጣችው ዕቅድ ሰብዓዊ ምግባር የጎደለው ነው" በማለት ኮንነውታል።

XS
SM
MD
LG