በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ባካሄደችው አዲስ ወረራ ሁለት ፍልስጤማውያንን ገደለች


ፍልስጤማውያን እስራኤል በዌስት ባንክ በሚገኝ የጃባ መንደር ባካሄደችው ወረራ ጉዳት የደረሰበትን መኪና ቆመው ሲመለከቱ - ጥር 14, 2023.
ፍልስጤማውያን እስራኤል በዌስት ባንክ በሚገኝ የጃባ መንደር ባካሄደችው ወረራ ጉዳት የደረሰበትን መኪና ቆመው ሲመለከቱ - ጥር 14, 2023.

እስራኤል ቅዳሜ እለት ዌስት ባንክ ውስጥ ባካሄደችው ወታደራዊ ወረራ ሁለት ፍልስጤማውያንን ተኩሳ መግደሏን እና ከሁለት ሳምንት በፊት ባደረገችው ተመሳሳይ ወረራ ቆስሎ የነበረ ሌላ ፍልስጤማዊም መሞቱን የፍልስጤም የህክምና ባለሙያዎች አስታወቁ።

ይህ ከእስራኤል ጋር የሚደረገው ደም አፋሳሽ ግጭት በዚህ አመት የተገደሉትን ፍልስጤማውያንን ቁጥር ወደ 11 ያሳደገው ሲሆን ባለፈው የፈረንጆቹ አመት የተነሳው ግጭት በዚህ አመትም የመብረድ ምልክት እንደማይታይበት ተዘግቧል።

የፍልስጤም የጤና ሚኒስትር ሟቾቹ ኢዘዲን ሀማምራ የተሰኘ የ24 አመት ወጣት እና አመጃድ ከህለለያህ የተሰኘ የ23 አመት ወጣት መሆናቸውን ያስታወቀ ሲሆን የ19 አመቱ ሳሚር አል-ጃባሪ ደግሞ ጥር ሁለት ቀን በተደረገ ግጭት በደረሰበት የመቁሰል አደጋ መሞቱን ገልጿል።

አልጃባሪ የቆሰለው የእስራኤል ወታደሮች የሁለት ፍልስጤማውያንን መኖሪያ ቤት ለማፍረስ ባካሄዱት ወረራ በደረሰ ግጭት ነው።

ፍልስጤማውያን በእስራኤል ላይ ባደረጉት ጥቃት 19 ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ እስራኤል ካለፈው የፀደይ ወቅት አንስቶ ወታደራዊ ወረራዋን አጠናክራ ቀጥላለች። እስራኤል የምታደርገው እንቅስቃሴ ወታደራዊ ትስስሮች ለማፍረስ እና ወደፊት ሊደርሱ የሚችሉ ጥቃቶችን ለማስቆም ነው ብትልም ፍልስጤማውያን ግን እስራኤል ለ55 አመት ስታካሂድ የቆየችው የመሬት ወረራ ቅጣያ አድርገው ይመለከቱታል።

XS
SM
MD
LG