በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ የናይሮቢውን ሽብር ጥቃት መሪ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አቀረበች


ዩናይትድ ስቴትስ በሽብር በተጠረጠረው ሞሃሙድ አብዲ ኤደን ዙሪያ መረጃ ለሰጠ ያቀረበችውን የ10 ሚሊየን ዶላር ሽልማት የሚያሳይ ፖስተር በናይሮቢ ተሰቅሎ ይታያል - ጥር 12, 2023
ዩናይትድ ስቴትስ በሽብር በተጠረጠረው ሞሃሙድ አብዲ ኤደን ዙሪያ መረጃ ለሰጠ ያቀረበችውን የ10 ሚሊየን ዶላር ሽልማት የሚያሳይ ፖስተር በናይሮቢ ተሰቅሎ ይታያል - ጥር 12, 2023

ዩናይትድ ስቴትስ እ.አ.አ በ2019 በናይሮቢ ሆቴል ላይ የተፈፀመው ጥቃት መሪ ነው የተባለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል መረጃ ለሰጠ እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

በኬንያ ዋና ከተማ በተፈፀመው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ዜጋን ጨምሮ 21 ሰዎች ሲሞት ሌሎች 30 ሰዎች ቆስለዋል።

ሞሃሙድ አብዲ ኤደን የተሰኘው ግለሰብ መቀመጫውን ሶማሊያ ያደረገው የአልሻባብ ታጣቂ ቡድን መሪ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጥቅምት ወር በይፋ በአሸባሪነት ፈርጆታል።

ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችውን የ10 ሚሊየን ዶላር ሽልማት ይፋ ያደረጉት በኬንያ የዩናይትድ ስቴት አምባሳደር ሜግ ዋይትማን እንደተናገሩት፣ አሜሪካ ኤደንን እና ሌሎች በሆቴሉ ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚረዳ ማንኛውንም መረጃ እየፈለገች ነው ብለዋል።

አሜሪካ ይፋ ያደረገችው የሽልማት ገንዘብ በሦስት ወራት ውስጥ ሦስተኛው ሲሆን በህዳር ወር ላይ - አህመድ ዲሪዬ፣ ሙሃድ ካራቴ እና ጀሃድ ሙስተፋ - የተሰኙ ሶስት የአልሸባብ መሪዎችን ለጠቆመ የ10 ሚሊየን ዶላር ሽልማት እንደምትሰጥ አስታውቃ ነበር።

XS
SM
MD
LG