በሩሲያ የሚደገፉ የክሬሚያዋ ሴቫስቶፖል ከተማ አገረ ገዥ ሚካኤል ራዛቮዜቭ ከዩክሬን የተላከ ነው ያሉት አንድ ሰው አልባ ድሮን አውሮፕላን የኦርቶዶክሱ የገና በዓል በሚከበርበት ዛሬ ቅዳሜ ተመቶ መወደቁን አስታወቁ።
ራዛቮዜቭ “ እነዚህ ሰብአዊነት የጎደላቸው ሰዎች በተቀደሰው የገና በዓል እንኳ ጀግናዋን ከተማችንን ከማጥቃት ሙከራቸው አልታቀቡም” ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሩሲያ ክሬሚያን ከዩክሬን በመንጠቅ ወደ ራሷ ግዛት የቀላቀለችው እኤአ በ20144 መሆኑ ተዘግቧል።
ዩክሬን ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ በፊት ወደ ግዛቷ የቀላቀለቻቸውንና ከወረራውም በኋላ የያዘቻቸውን ግዛቶችዋን እንደምታስለቀቅ አስታውቃለች።
ሴባስቶፖል ሩሲያ በጥቁር ባህል የምታንቀሳቅሳቸው የባህር ትራንስፖርቶችዋ መናኻሪያ መሆናዋ ተመልክቷል።
በተያይዘ ዜናም የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የገናን በዐል ዋዜማ ሌሊቱን ክሬምሊን ውስጥ በሚገኘው ካቴድራል ማክበራቸው ተነገሯል።
ፑቲን ለሩሲያው ኦሮቶዶክስ የገና በዓል 36 ሰዐት የሚቆይ የተኩስ ማቆም ያወጁ ቢሆንም ውጊያው ግን እየቀጠለ መሆኑን የብሪታኒያው መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።