በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመጨረሻም መካርቲ አፈጉባኤነቱን አሸነፉ


የካሊፎርኒያው እንደራሴ ኬቭን መካርቲ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።
የካሊፎርኒያው እንደራሴ ኬቭን መካርቲ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

በአምስት ቀናት፣ ለ15 ዙሮች ድምጽ ከተሰጠ እና ከቀኝ አክራሪዎቹ የሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ጋር ከተደረገ ድርድር በኋላ የካሊፎርኒያው እንደራሴ ኬቭን መካርቲን ዛሬ ቅዳሜ አጥቢያውን የዩናይትድ ስቴትስ አፈጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ለመከርቲ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት ልከዋል። “ ከሪፐብሊካኖች ጋር አብሬ መስራት በምችልበት አጋጣሚ ሁሉ አብሮ ለመሰራት ዝግጁ ነኝ ፣ መራጮችም ሪፐብካኖቹ ከኔጋር እንዲሰሩ ይፈልጋሉ" ብለዋል ባይደን።

ትናንት አርብ ለ14ኛው ጊዜ የተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ በኋላ ወደ ሰኞ እንዲተላለፍ የቀረበው ሀሳብ በምክር ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። በመጨረሻም ሪፐብሊካኖቹ ስልታቸውን በመቀየር ለ15ኛ ጊዜ አዲስ መሪ ለመምረጥ በተደረገ ጥረት አፈጉባኤውን መምረጥ ችለዋል።

ቀደም ባሉት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቶች 20 የሚሆኑ የተቧደኑ የሪፐብሊካን የቀኝ ክንፍ ወግ አጥባቂ እንደራሴዎች መካርቲ እንዳይመረጡ ተከላክለው መቆየታቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ መካርቲ በዩናይትድ ስቴትስ ህገመንግሥት መሰረት ፕሬዚዳንቱና ምክትል ፕሬዚዳንቱ በማይኖሩበት ወቅት የመሪነቱን ስልጣን መረከብ ከሚያስችለው የአፈጉባኤነቱ እጩነት ራሳቸውን እንደሚያገልሉ ፍንጭ አልሰጡም። ሪፐብሊካኖችም አፈጉባኤነቱን አሳልፎ ለመስጠት ስለማሰባቸው ምልክት አላሳዩም።

የ57 ዓመቱ መካርቲ የአፈጉባኤነቱን ስፍራ ለዓመታት ሲመኙት መቆየታቸው ሲነገር ባላፉት በርካታ ሳምንታትም የሪፐብሊካኖቹ ባላንጣዎቻቸውን ድጋፍ ለማግኘት በተደጋጋሚ ሲያገኝዋቸው እንደነበር ተገልጿል።

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ ዴሞክራቱ ቻክ ሹመር “መካርቲ የተመኙት የሥራ ኃላፊነት ለአሜሪካ ህዝብ ወደ ሰቀቀንነት ሊቀየር ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ምክንያቱም “መካርቲ የግድ አስፈላጊው የሆነውን ድምጽ ለማግኘት ራሳቸውን ፈጽሞ እንግዳ ለሆኑ የሪፐብሊካኑ ፓርቲ አባላት ሊያንበረክኩ ይችላሉ“ ብለዋል ሹመር።

ሹመር አክለውም የመካርቲ ለጽንፈኞቹ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት መገበር “አሜሪካን እንደገና ታላቅ እናድርጋት” በሚል ምክር ቤቱን የተቆጣጠሩት ሪፐብሊካኖች፣ መንግሥት እንዲዘጋ ወይም አገሪቱን ወደ ከፍተኛ ጦስ ወደሚከት ውድቀት እንድትገባ ሊያደርጓት ይችላሉ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG