በደቡብ ኦሮምያ ክልል በሁለቱ ጉጂ ዞኖች ውስጥ ያለው የፀጥታ ችግር ለተረጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ አዳጋች እንዳደረገበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ አስታወቀ።
በክልሉ ያለዉ የሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የገለፀው ድርጅቱ፤ ባለው የፀጥታ ችግር ተረጅዎችን መድረስ እንዳልተቻለም ዘርዝሯል።
ከምዕራብ ጉጂ ዞን ወረዳዎች ተፈናቅለዉ ላላፉት ሁለት ዓመታት በዞኑ ዋና ከተማ ቡሌ ሆራ ተጠልለዉ የሚገኙ ተፈናቃዮች እንደተናገሩት፣ በመንግሥት እየቀረበላቸው ያለው እርዳታም እንደሚዘገይ ተናግረዋል።
/ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/