በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆ ባይደን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ዕጩ አምባሳደር አቀረቡ


በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት ሚኒስትር ኧርቭን ማሲንጋ
በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት ሚኒስትር ኧርቭን ማሲንጋ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያ ለሚገኘው አሜሪካ ኢምባሲ በሙሉ አምባሳደርነት የሚያገለግሉ ዕጩ አምባሳደር አቀረቡ።

ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ታኅሣስ 25/ 2015 ዓ.ም በዋይት ሃውስ በኩል ለዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር በተላከው ዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ በኢትዮጵያ ሙሉ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረቡት ኧርቭን ማሲንጋ ይገኙበታል።

ኧርቭን በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ረዳት ሚኒስትር ናቸው።

በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ከአንድ ዓመት በፊት በጡረታ ሲሰናበቱ በምትኩ በጉዳይ ፈፃሚነት የተሾሙት አምባሳደር ትሬሲ ጄከብሰን መሆናቸው ይታወቃል።

ጆ ባይደን ያቀረቡት አዲስ ሹመት ከፀደቀም በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ሙሉ ሥልጣን ያለው አምባሳደር ያገኛል ማለት ነው።

XS
SM
MD
LG