በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ ፕሬዚዳንት የደህንነት መግለጫ የተደባለቀ ምላሽ ስቧል


የሶማልያ ፕሬዚዳንት የደህንነት መግለጫ የተደባለቀ ምላሽ
ስቧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

የሶማልያ ፕሬዚዳንት የደህንነት መግለጫ የተደባለቀ ምላሽ ስቧል

የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሀሙድ አዲሱን የአውሮፓውያን ዓመት አስመልክቶ ባላፈው እሁድ ባሰሙት ንግግር ሀገራቸው የአልሸባብ እስላማዊ ሚሊሺያዎችን በዚህ ዓመት እንደምትደምሰስ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባላፈው ዓመት አልሸባብ ላይ ያወጁት ሁሉን አቀፍ ጦርነት አማጽያኑን እየገፋ ይቆጣጥሯቸው ከነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች በማስለቀቅ ስኬት አስመዝግቧል፡፡ ሶማልያ ደህንነት የማስከበሩን ሥራ ከአፍሪካ ኅብረት ሰላም አሰከባሪዎች እጅ በዚህ ዓመት ትረከባለች ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የሶማልያ ብሄራዊ ጦር፣ በማዕከላዊ ሶማልያ በሚገኙ የአካባቢ ሚሊሻዎች እርዳታ አልሸባብ ላይ በቅርብ ያስመዘገባቸው ድሎች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል፡፡

የሶማልያ ፕሬዚዳንት መሀሙድ ባሰሙት ንግግር ከእስልምና መንገድ የወጡ ወይም “ከዋሪጅ” ሲሉ የጠሩትን አልሸባብን ለማጥፋት ሶማሊያዊያን ከጎናቸው እንዲቆሙ ጠይቀዋል፡፡

“የትም ቦታ የሚኖሩ ቢሆንም ሶማሊያዊያን በከዋሪጅ ላይ አቋም ወስደዋል፡፡ ይህ ይጦርነት ለውጥ እያመጣ ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል፡፡ በ2023 ሶማልያ የበለጸገች እና ሰላማዊ እንድምትሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና አሁን ሶማልያ ላይ ያተኮረው የአፍሪካ ቀንድ የፖሊሲና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር፣ አህመድ አብዲሰላም፣ ፕሬዚዳንቱ መንግሥታቸው የደህንነቱን ሥራ ከአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪዎች እጅ እንደሚወስድ መናገራቸውን ደግፈዋል፡፡

“ደህንነት ያገሪቱ ቁልፍ ጉዳይ እስከሆነ ድረስ የፕሬዚዳንቱ ዓመታዊ ንግግር ተቀባይነት ሊያገኝ ይገባል፡፡ ደህንነትን አስመልክቶ ፕሬዚዳንቱ ኃላፊነቱን የወሰዱበትን ጊዜ ለማመላከት የእቅዳቸውን የጊዜ ሰሌዳ ማመልከታቸው ትልቅ ነገር ነው፡፡”ሲሉ አብዲሰላም ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ ሞቃድሾ ውስጥ የሚገኙት የፖለቲካ ተንታኙ አብዱላሂ ጋፎው የፕሬዚዳንቱን ንግግር አስመልክቶ ጥርጣሬ ያላቸው መሆኑን ሲገልጹ

“የፕሬዚዳንቱን ንግግር ከሰማሁ በኋላ በአሁኑ እና የቀድሞዎቹ ፕሬዚዳንቶች በሰጧቸው ንግግሮች መካከል ምንም ልዩነት አላየሁም፡፡” ብለዋል፡፡ “ደህንነቱን አስመልክቶ ሁሉም ፕሬዚዳንቶች ከአፍሪካ ህብረት ላይ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ የተለወጠ ነገር የለም፡፡ “ ሲሉም ተንታኙ አክለዋል፡፡

ጋፎው፣ የአፍሪካ ህብረት ኃይሎች ከሶማልያ መውጣት፣ አሁን ድረስ በተባበሩት መንግሥታት የመሳሪያ ማእቀብ ስር ባለችው ሶማልያ ሁኔታዎችን የበለጠ ያወሳስበዋል፡፡” በማለት “ይህ ደግሞ ለሶማልያ የደህንነት ኃይሎች አቅምን ለመገንባት መሰናክል ይሆናል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሰላም አሰከባሪ ኃይሎች እኤአ ከ2007 ጀምሮ ጠንካራ የመንግሥት ይዞታዎችን አስከብረው መቆየታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG