በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዩክሬን ጥቃት የተገደሉት ወታደሮቿ ቁጥር 89 መድረሱን ተናገረች


ማኪይቭካ
ማኪይቭካ

የዩክሬን ኃይሎች በምስራቅ ዩክሬን ሩሲያ በያዘችው ከተማ በሚገኘው ወታደራዊ ሰፈር ላይ ባካሄዱት ጥቃት ከባድ ጉዳት የደረሰው ሩሲያ ወታደሮቿ በሚኖሩበት አቅራቢያ የጥይት እና የሌላም ተተኳሽ ክምችት ስለነበራት ሊሆን እንደሚችል ብሪታኒያ ተናገረች።

የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ በትዊተር ባሰፈረው ግምገማው የደረሰው ጉዳት ከባድ ያደረገው፣ "በመሳሪያ እና ጥይት መጋዘኑ ላይም ፍንዳታ በመድረሱ ሳይሆን አልቀረም" ብሏል።

አያያዞም ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯም አስቀድሞ የጥይት ክምችቶችን አደጋ በማያደርስ መንገድ ያለማስቀመጥ ልማድ እንዳላት ይታወቃል ያለችው ብሪታኒያ "ይህ ተገቢ ያልሆነ አሰራሯ በሰዎቹዋ ላይ ከባድ ጉዳት እንዲደርስ አስተዋጽኦ አለው" ስትል አክላለች።

የሩሲያ ጀነራል ሴርጌይ ሰቭሪዩኮቭ በጥቃቱ የተገደሉት ወታደሮች ቁጥር ከ63 ወደ 89 ከፍ እንዳለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG