በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቀይ መስቀል ለትግራይ ክልል 10 አምቡላንሶች በሥጦታ አበረከተ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ዛሬ በመቀሌ 10 አምቡላንሶች እና ሌሎች 5 ተሽከርካሪዎችን አበርክቷል።

በርክክቡ ሥነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ፕሬዚዳንት እና የትግራይ ክልል የቀይ መስቀል ቅርንጫፍ እና የክልሉ የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አምቡላንሶቹ ታካሚዎች ላይ በመጓጓዣ ዕጦት ሲደርስ የቆየውን ከባድ ችግር ለመቅረፍ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ባለሥልጣናቱ ጠቅሰዋል።

የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አማኑኤል ኃይሌ የመጡት አምቡላንሶች በተለይ የማዋለድ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ነፍሰ ጡር ሴቶች ለማጓጓዝ እንደሚረዱ ገልጸው፣ "ተጨማሪ አምቡላንስ ይመጡልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG