በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል ጤና ተቋማት ይዞታ


የትግራይ ክልል ጤና ተቋማት ይዞታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:06 0:00

የትግራይ ክልል ጤና ተቋማት ይዞታ

በመቀሌ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኝ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ላለፉት ሁለት ዓመታት ለካንሰር ሕክምና የሚያገለግል መድኃኒት ባለመግባቱ ታካሚዎች ለሞትና እንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ማዕከሉ ገለፀ።

“በሕገ ወጥ መንገድ የሚገቡ አንዳንድ መድኃኒቶች ገዝተን ለመጠቀም ዋጋውም ውድ ሆኗል” ሲሉ ታካሚዎች ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በሆስፒታሉ ተቋርጦ የነበረው የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር አይሲአርሲ ባደረገው እርዳታ በዚህ ሳምንት ዳግም መጀመሩ ተነግሯል።

የክልሉ ጤና ቢሮ በበኩሉ የጤና ሥርዓቱ በከፍተኛ ደረጃ በጦርነቱ መጎዳቱን ገልፆ መጠኑ አነስተኛ ቢሆንም አሁን ግን የእርዳታ መድኃኒት ወደ ክልሉ መግባት መጀመሩን ተናግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG