በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"እስራኤል ባካሄደችው የሚሳይል ጥቃት የደማስቆ አውሮፕላን ማረፊያ መትታለች" ስትል ሶሪያ አስታወቀች


ፎቶ ፋይል፦ ደማስቆ
ፎቶ ፋይል፦ ደማስቆ

እስራኤል ዛሬ ሰኞ ባካሄደችው የሚሳይል ጥቃት የደማስቆ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያን መትታ ከአገልግሎት ውጪ አድርጋዋለች ሲሉ የሶሪያ ወታደራዊ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የሶሪያ የጦር ኃይል ባወጣው መግለጫ ዛሬ ንጋት ላይ የተካሄደው የሚሳይል ጥቃት ደቡባዊ ደማስቆ ያሉ ሌሎች ዒላማዎችንም መደብደቡን እና ሁለት ወታደሮች መገደላቸውን አመልክቷል።

እስራኤል የሶሪያ መንግሥትን መግለጫ አስመልክታ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠችም። የሆነ ሆኖ ካለፉት ቅርብ ዓመታት ጀምሮ ሶሪያ ውስጥ ያሉ ዒላማዎችን በተደጋጋሚ እየደበደበ የሚገኘው የእስራኤል የጦር ኃይል ሄዝቦላን የመሳሰሉ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች ሶሪያ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ለመከላከል የሚወስደው ዕርምጃ እንደሆን ይናገራል።

ባለፈው ሰኔ ወር እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት የደማስቆ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያ ለሁለት ሳምንታት ተዘግቶ እንደነበር ይታወሳል።

በመስከረም ወር አሌፖ በሚገኘው የአውሮፕላን ጣቢያ ላይ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት ጣቢያው ለበርካታ ቀናት ከአገልግሎት ወጭ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG