በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ በአዲሱ ዓመት የሰላም ጥሪ አደረጉ


ጎማ፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ
ጎማ፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ

አሮጌው የአውሮፓዊያን ዓመት 2022 ሲገባደድ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ለመላው ዓለም መልዕክት አስተላልፈዋል። ጉቴሬዥ በ2023 የአለም ዜጎች ሰላምን የቃላቸው እና የተግባራቸው ማጠንጠኛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የጎሮጎሮሳዊያኑ 2022 ክስተቶችን እና ተግዳሮቶችን የገመምገሙት ዋና ጸሃፊው ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት መልዕክት “በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የአሮጌውን ዓመት መከራ እና አመድ አራግፈው ጥለዋል” ያሉ ሲሆን አዲሱን ዓመትም አዲስ ንጋት እና ብሩህ ቀን ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

“ከዩክሬን እስከ አፍጋኒስታን፣ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ እና ከዚያም ባሻገር ሰዎች የተሻለ ነገር ፍለጋ የፈራረሰ ቤታቸውን ጥለው ተሰደዋል” ያሉት ዋና ጸሃፊው፤ “በዓለም ዙሪያ አንድ መቶ ሚሊዮን ሰዎች ጦርነትን፣ ሰደድ እሳትን፣ ድርቅን፣ ድህነትን እና ረሃብን ሸሽተው በስደት ላይ ናቸው” ብለዋል። በመጪው በ2023 ከምንግዜውም በላይ ሰላም እንፈልጋለን ሲሉም አሳስበዋል።

ግጭቶች እንዲወገዱም ሰላምን በውይይት ማረጋገጥ እንደሚቻልም ያስታወሱ ሲሆን ከተፈጥሮና ከአየር ንብረት ጋር ሰላም በመፍጠር ዘላቂነት ያለው ዓለም ማምጣት እንደሚቻልም ተናግረዋል። ሴቶች እና ልጃገረዶች በክብር እና በደህንነት መኖር እንዲችሉ በቤት ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG