በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የሮማ ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳስ ቤኒዲክት በ95 ዓመታቸው ሞቱ


የሊቀ ጳጳስ ቤኔዲክት መታሰቢያ
የሊቀ ጳጳስ ቤኔዲክት መታሰቢያ

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ለስምንት ዓመታት ያህል በርዕሰ ሊቃነ-ጳጳስነት የመሩት ሊቀ-ጳጳስ ኤሜሪተስ ቤኔዲክት በ95 ዓመታቸው ዛሬ ቅዳሜ ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋገጧል። ሊቀ-ጳጳስ ቤኔዲክት ከ16ኛው መቶ ከፍለ ዘመን፤ ከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ ሥልጣናቸውን የለቀቁ የመጀመሪያው ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳስ ናቸው።

የሊቀ-ጳጳስ ቤኔዲክት የጤና ሁኔታ ‘በእርጅና ምክንያት’ ከዕለት ወደ እለት እየተዳከመ መምጣቱን በመግለጽ ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ ለቀድሞ ሊቀ-ጳጳስ እንዲጸልይ ጥሪ አቅርበው ነበር።

ቫቲካን የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳስ አስክሬን ከሰኞ ጀምሮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ እንደሚገኝ አስታውቃለች። ርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ፍራንሲስ ቤኔዲክት የቀብር ሥነ-ሥርዓት የፊታችን ሐሙስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይፈጸማል።

ሊቀ-ጳጳስ ቤኔዲክት እ.ኤ.አ. በ 2013 ከስልጣን እንደሚለቁ ሲያስታውቁ ዜናው አስደንጋጭ ሆኖ ነበር። ሊቀ-ጳጳስ ቤኔዲክት እንደ ርዕሰ ጳጳስነት የማገልገል አካላዊ እና አዕምሮአዊ ጥንካሬ እንደሌላቸው በወቅቱ ተናግረው ነበር።

የመጨረሻዎቹን የጡረታ ዘመናቸውንም በቫቲካን በሚገኝ ጥንታዊ ገዳም ውስጥ በመሆን ጊዜያቸውን ለጸሎት እና ለጥሞና በመስጠት ከሕዝብ ፊት ርቀው ኖረዋል።

XS
SM
MD
LG