ሶማሊያን ባጠቃት እጅግ ከባድ ድርቅ ከሁሉም በላይ የተጎዱት ሴቶች እና ልጃገረዶች መሆናቸውን የረድዔት ሠራተኞች ይናገራሉ። በግማሽ ምዕተ ዓመት ባልታየ ደረጃ አስከፊ በሆነው ድርቅ ምክንያት ሴቶች እና ልጃገረዶች ለፆታዊ ጥቃት እየተጋለጡ እና ልጃገረዶች እንዲያቆሙ እየተደረጉ መሆኑን የረድዔት ሠራተኞቹ አስታውቀዋል።አዋቂ ሴቶች እና ልጃገረዶቹ ውሃ ለመቅዳትም ሆነ ትምህርት ቤት ለመሄድ ረጅም መንገድ በእግር ስለሚጓዙ ለጥቃት ይጋለጣሉ።
/ጁማ ማጃንጋ ከሶማሊላንድ ቶጎድሂር ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/