በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁዋዌ 'ከነበርኩበት ቀውስ ወጥቻለሁ' ሲል አስታወቀ


የሁዋዌ መደብር በቤጂንግ
የሁዋዌ መደብር በቤጂንግ

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ሽያጩ ለዓመታት ተወስኖ እንዲቆይ እገዳ የጣለችበት ግዙፉ የቻይና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ “በንግድ ቀውስ ውስጥ” የመሆኑ ሁኔታ ማብቃቱን አስታወቀ፡፡

“የዩናይትድ ስቴትስን እገዳዎች አሁን ተለማምደናቸዋል እንደ ወትሮው ወደ መደበኛው የንግድ ይዞታችን ተመልሰናል” ሲሉ የኩባንያ የወቅቱ ሊቀመንበር ኤሪክ ሹ ዛሬ ዓርብ ባወጡት መግለጫቸው ገልጸዋል፡፡

የ2022 ዓመታዊ ገቢው 91.6 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ያስታወቀው ሁዋዌ የዘንድሮ ገቢው ካለፈው ዓመት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

መሰረቱን በቤጂንግ ያደረገው የኤሌክትሮኒክስ ኢንደስትሪ ተንታኝ ሊ ቼንግዶንግ “ሁዋዌ በቀውስ ውስጥ ሆኖ እያለፈ ማደግና ማትረፍን የተካነበትና ብዙ ልምድ ያካበተ ድርጅት መሆኑ ይሰማዋል” ሲሉ ለቪኦኤ የማንደሪን ቋንቋ አገልግሎት ተናግረዋል፡፡

“ስለዚህ አሁንም ብዙ አዳዲስ ቢዝነሶችን በመፍጠር በንቃት ለመንቀሳቀስ ብሩህ ተስፋ ያለው ድርጅት ነው” በማለትም ባለሙያው የድርጅቱን እምነት ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት ሁዋዌ እኤአ በ2019 የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድርጅቱ ቻይና የዩናይትድ ስቴትስን ለመሰለል የምትጠቀምባቸውን ቴክኖሎጂዎች ያመቻቻል በሚል እቀባ የጣሉበት መሆኑን ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG