በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን 750 ወታደሮቿን ወደ ኮንጎ ላከች


የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ወደ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለመሄድ ጁማ በሚገኘው የሰራዊቱ ዋና መቀመጫ ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ - ታህሳስ 28፣ 2022 (Sheila Ponnie/VOA)
የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ወደ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ለመሄድ ጁማ በሚገኘው የሰራዊቱ ዋና መቀመጫ ዝግጅታቸውን ሲያጠናቅቁ - ታህሳስ 28፣ 2022 (Sheila Ponnie/VOA)

ደቡብ ሱዳን በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሠላምን ለማስፈን የተሠማራውን ጦር የሚቀላቀሉ 750 ወታደሮች ዛሬ ሸኝታለች።

ደቡብ ሱዳን ወታደሮቿን የምሥራቅ አፍሪካውን ኃይል እንዲቀላቀል የምትልከው የእራሷን ሠላም ለመጠበቅ ባልቻለችበት ሁኔታ ነው።

በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለአስርት ዓመታት የቆየውን ሁከት ለማብረድ የተሠማራውን የምሥራቅ አፍሪካ ጦር እንዲቀላቀል ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ያሰማሯቸው ወታደሮች ከኬንያ፣ ቡሩንዲ፣ እና ኡጋንዳ የተውጣጣውን ጦር ይቀላቀላሉ።

ከጉዟቸው በፊት ጁባ በተደረገው የሽኝት ሥነ-ሥር ዓት ላይ ወታደሮቹ ሙያቸው የሚጠብቀውን ለማድረግ እንዲጥሩ ፕሬዝደንት ኪር መክረዋቸዋል። እንደ አስገድዶ መድፈር የመሠሉ ወንጀሎችን እንዳይፈጽሙም አበክረው መክረዋል።

የደቡብ ሱዳን ወታደሮቹ በጎማ ከተማ የሚመደቡ ሲሆን በዛም ፀጥታን ያስከብራሉ ተብሏል።

በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የአገሪቱ ጦር ከኤም-23 አማጺያን ጋር 10 ዓመት የቆየ ግጭት ውስጥ ሲሆን ኤም 23ን ሲቪሎችን በማጥቃት ይከሰሳል።

XS
SM
MD
LG